“በያይነቱ” የተሰኘ የኪነጥበብ ዝግጅት የፊታችን ሐሙስ ሕዳር 18 2018 ዓ.ም ያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት አሸናፊ ከበደ አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።
በዝግጅቱ ላይ ግጥም፣ ወግ፣ሙዚቃ፣ ሞኖሎግ፣መልቲሚዲያ ቴአትር፣ ላይቭ ፔንቲንግ ይቀርባሉ።
ድምፃዊ አረጋኸኝ ወራሽ፣ አርቲስት ዳንኤል ተገኝ እንዲሁም ሰአሊና ቀራፂ በቀለ መኮንን የክብር እንግዳ በመሆን ተገኝተው ልምዳቸውን ያካፍላሉ።
ዝግጅቱ በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የቴአትር እና ፊልም ጥበባት ፣ የያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት እና የአለ ስነ የጥበብ እና ዲዛይን ተማሪዎች የተዘጋጀ ነው።
