ከመጠን በላይ መረጃ የመቀበል አደጋ

Date:

በአሁኑ የዲጂታል ዘመን በየቀኑ የምናስተናግደው የመረጃ ብዛት አዕምሯችን ሊሸከመው ከሚችለው በላይ እየሆነ መጥቷል። ይህ ሁኔታ በሳይንሱ “Cognitive Overload” ይባላል።

አዕምሯችን በአንድ ጊዜ ሊያከናውነው የሚችለው ተግባር ውስን በመሆኑ ተደራራቢ መረጃዎችን ስንጭንበት የሚፈጠር ችግር ነው።

መረጃዎች በበዙ ቁጥር ደግሞ አዕምሯችን በጥልቀት ማሰብ የሚችልበትን በቂ ትኩረት ያጣና በትንንሽና በማይረቡ መረጃዎች እንዲወጠር ይደረጋል። ይህ ደግሞ በዕለት ተዕለት ሥራችን ላይ ትኩረት እንድንነፈግና አዕምሯችን እንዲዝል በማድረግ ለከፍተኛ ድካም ይዳርገናል።

በተጨማሪም፥ መረጃ በበዛ ቁጥር ትክክለኛ ውሳኔ የመወሰን አቅማችን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀንስ ጥናቶች ያሳያሉ።

አዕምሯችን “Analysis Paralysis” በሚባለው ደረጃ ላይ ሲደርስ፣ ብዙ አማራጮችና መረጃዎች ስላሉት ብቻ ግራ ተጋብቶ ምንም ዓይነት ውሳኔ መወሰን ያቅተዋል።

በተለይ ደግሞ የምንቃወማቸው ሰዎች ወይም የማንደግፈው ሀሳብ ተደጋግሞ ሲቀርብልን፣ አዕምሯችን መረጃውን ከመተንተን ይልቅ ራሱን ወደ መከላከል ስሜት ስለሚያስገባ ለጭንቀትና ለውሳኔ ማጣት ይዳረጋል።

ይህ የአዕምሮ ውጥረት ( Cognitive Overload) የፈጠራ ችሎታችንን ከመግደሉም በላይ፣ አዕምሯችን በአንድ ነገር ላይ ሳይረጋ “ስታክ” ሆኖ እንዲቀር ያደርገዋል።

ብዙዎቻችን ረጅም ሰዓት በማይመለከተን ነገር ላይ የምናሳልፈውም አዕምሯችን መረጃን የመለየት አቅሙ ስለሚዝልና በቀላሉ በሚገኙ የ”ዶፓሚን” ሆርሞን አነቃቂዎች ስለሚታለል ነው።

ሰዓታችንን በማይመለከተን መረጃ ላይ የምናጠፋው አዕምሯችን በቂ መረጃ ስለሚያገኝ ሳይሆን፣ ጥራት ያለው መረጃ የመምረጥ አቅሙ ስለደከመ መሆኑን መረዳት ይገባል።

ስለዚህ የአእምሮ ጤናንና ሰላምን ለመጠበቅ፣ የሚመጣውን መረጃ ሁሉ ከመቀበል ይልቅ የሚጠቅመውን መምረጥ ግድ ይላህ።

በተጨማሪም አዕምሮ አረፍ ብሎ መረጃዎችን የሚያቀነባብርበት ጊዜ መስጠት ወሳኝ መሆኑን ሳይንሱ ይመክራል።

እናንተስ እንደዚህ አይነት ስሜት ውስጥ ገብታችሁ ታቃላችሁ ?

Source : BBC Worklife, Vocal

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...