የተመድ ዋና ጸሐፊ አስጠነቀቁ

Date:

የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፤ የመካከለኛው ምሥራቅ ሁኔታ “ከዚህ በላይ አሳሳቢ ሊሆን አይችልም” ሲሉ እየተባባሰ የመጣው ግጭት እንዲቆም ጠየቁ።

ዋና ጸሐፊው ኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት፤ “በመካከለኛው ምሥራቅ እና ከዚያም ባሻገር የሚፈጸሙት ሕገ ወጥ ጥቃቶች በመላው ቀጣናው የሚገኙ ንጹኃን ላይ ከፍተኛ ስቃይ እና ጉዳይ እያደረሱ ነው” ብለዋል።

የቀጣናው ሁኔታ፤ “ለዓለም ኢኮኖሚ፤ በተለይም ተጋላጭ በሆኑ ወገኖች ላይ አስከፊ ስጋት ደቅኗል” ሲሉም አሳስበዋል።

“ሁኔታው ከሁሉም ቁጥጥር ውጪ በሆነ ሁኔታ ሊባባስ ይችላል። ውጊያውን አቁሞ ወደ ተጨባጭ የዲፕሎማሲ ንግግር ለመግባት ጊዜ አሁን ነው። [ሁኔታው] ከዚህ በላይ አሳሳቢ ሊሆን አይችልም” ሲሉም አስጠንቅቀዋል።

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ጉዳዮች እና የአደጋ ጊዜ እርዳታ ምክትል ዋና ጸሐፊ የሆኑት ቶም ፍሌቸር በበኩላቸው፤ ለጦርነቱ እየዋለ ስላለው “ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ” አንስተዋል።

“ፖለቲከኞች እርዳታ ለሚሹ ወገኖች የሚውለውን በጀት በማቋረጥ በሚወስዱት እርምጃ መኩራራታቸውን” የጠቀሱት ፍሌቸር፤ መሪዎቹ ለጦርነት ገንዘብ እያዋሉ መሆኑን በማንሳት ወቅሰዋል።

አክለውም፤ “ገዳይ የሆነ ቴክኖሎጂ ላይ እና ያለ ተጠያቂነት የሚፈጸመው ግድያን በተመለከተ ያለው ኅብረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሆኑን እየተመለከትን ነው” ብለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...