የተሽከርካሪዎች በካይ ጋዝ ልቀት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለጸ

Date:

በአዲስ አበባ ከተማ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች የሚለቁት በካይ ጋዝ ለነዋሪዎች ጤና፣ በተለይም ለሕፃናትና ለአረጋውያን ከፍተኛ ስጋት እየደቀነ መሆኑን የከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው በቅርቡ ባደረገው ድንገተኛ የልኬት ምርመራ ከተመረመሩ 75 ተሽከርካሪዎች መካከል ሲሶ የሚሆኑት ከተፈቀደው መጠን በላይ ጋዝ እንደሚለቁ አረጋግጧል።

ይህ የብክለት ችግር በግል ተሽከርካሪዎች ላይ ብቻ ሳይወሰን በመንግሥት ተቋማት መኪኖች ላይም የታየ ሲሆን፣ ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ “የተሽከርካሪ በካይ ጋዝ ልቀት ቁጥጥር መመሪያ ቁጥር 1051/2017” ተፈጻሚ መደረግ ጀምሯል።

በተጨማሪም የትራንስፖርት ቢሮው የተሽከርካሪ ምርመራ ተቋማት (ቦሎ ሰጪዎች) ከሙስና በጠራ መልኩ ሙያዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥብቅ ማሳሰቢያ አስተላልፏል።

በአሁኑ ወቅት የከተማ አስተዳደሩ በስሩ የሚገኙ ተሽከርካሪዎች የጋዝ ልቀትን የሚቀንሱ ቴክኖሎጂዎችን እንዲገጥሙ ግዴታ የጣለ ሲሆን፣ የግል ባለቤቶችም መሰል እርምጃዎችን እንዲወስዱ ጥሪ ቀርቧል።

ይህም የከተማዋን የአየር ጥራት ለማሻሻልና በካይ ጋዝ የሚያስከትለውን የጤና እክል ለመቀነስ የታለመ የተቀናጀ ጥረት አካል መሆኑ ተመላክቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...