ደቡብ ኮሪያ በትምህርት ቤቶች ስልክ ከለከለች

Date:

ደቡብ ኮሪያ በትምህርት ቤቶች ውስጥስልክ መያዝ የሚከለክለውን ረቂቅ ሕግ አጸደቀች።

ሕጉ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን እና ዘመናዊ የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎችን በክፍል ውስጥ መያዝን የሚከለክል ሲሆን፥ በህጻናትና ታዳጊዎች ላይ ይህን መሰሉን ሕግ በመተግበር ቀዳሚ ሆናለች።

ከቀጣዩ መጋቢት ወር የትምህርት ዘመን ጀምሮ የሚተገበረው ይህ ሕግ፥ የተንቀሳቃሽስልክ ሱስን ለመቀነስ ያለመ መሆኑን ቢቢሲ አስነብቧል።

ህግ አውጪዎች ታዳጊ ህጻናት ዘመናዊ ስልክ አብዝተው መጠቀማቸው የጥናትና የእረፍት ሠአታቸው ላይ ተፅዕኖ በመፍጠር የትምህርት አቀባበላቸውን ይጎዳል በሚል ሕጉን ይደግፋሉ።

ተማሪዎች በአንጻሩ የችግሩን ስረ መሰረት መመልከት ይሻላል በሚል አተገባበሩችግር ይፈጥራል በሚል አሁንም እየተቃወሙ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...