ፍሬሕይወት ታምሩ የ2026 የአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴት የቢዝነስ መሪዎች እውቅና አገኙ

Date:

ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ መቀመጫውን በእንግሊዝ ለንደን ከተማ ባደረገው አፍሪካ ቢዝነስ መጽሔት የ2026 የአፍሪካ ሴት የቢዝነስ መሪዎች (African Business Women in Leadership 2026) መካከል በመሆን እውቅና ማግኘታቸውን ኩባንያው ገልጿል።

ይህ ዕውቅና በተለይም ባለፉት ዓመታት በሀገራችን በቴሌኮም እና በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዘርፍ ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ላስመዘገቡት የላቀ ስኬት እና ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ትልቅ ተምሳሌት ሆኖ የተሰጠ ዓለም አቀፍ እውቅና ጭምር ነው።

በዋና ሥራ አስፈጻሚዋ በሳል የለውጥ አመራር ብቃት፣ ኩባንያችን ከመደበኛ የቴሌኮም አገልግሎት ባሻገር ወደ ሁለገብ የዲጂታል ተጠቃሚነት እና የኢኮኖሚ እድገት ጉልህ ሚና የሚጫወት ዋና ሞተርነት መሸጋገር ችሏል።

በተጨማሪም የኩባንያው “ቀጣዩ አድማስ፡ ዲጂታልና ከዚያም ባሻገር 2028” ስትራቴጂን በመቅረጽ እና ተግባር ላይ በማዋል፣ ተቋምን በተሳካ ሁኔታ መምራት ብቻ ሳይሆን ለሀገራችን የዲጂታል መጻኢ ዕድል ፅኑ መሠረት በማስቀመጥ ላይ ይገኛሉ፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...

የኢትዮጵያ አጠቃላይ ብድር 51.8 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ይፋ ሆኗል

ኢትዮጵያ  በድጋፍ መልክ ከአሜሪካ በየዓመቱ  በመንግስት በኩል ፈሰስ የሚደረግ...