የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን እና የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በቀጣዩ ሳምንት በሚካሄደው የቻይና ግዙፍ ወታደራዊ ትርኢት ላይ ከሚገኙ ከሃያ በላይ የውጭ ሀገር መሪዎች መካከል እንደሚገኙ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሀሙስ ዕለት አስታውቋል።
በቤጂንግ ቲያናንመን አደባባይ በመስከረም 3 ቀን የሚካሄደው ትርኢት፣ ጃፓን በይፋ እጇን ከሰጠች በኋላ የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ 80ኛ ዓመትን ለማክበር በቻይና በሚደረጉ በዓላት ውስጥ አንዱ አካል ነው።
ፑቲን እና ኪም፣ በዢ የእንግዳ ዝርዝር አናት ላይ መቀመጣቸውን ይፋ ያደረገው የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ሶስቱ መሪዎች በቤጂንግ የሰማያዊ ሰላም በር አናት ላይ ጎን ለጎን ቆመው የአንድነት ምልክት የሚያሳዩበት እጅግ አስደናቂ መድረክም ተዘጋጅቷል።
የሰሜን ኮሪያው የመንግስት የዜና ወኪል ኬሲኤንኤ (KCNA) ኪም በበዓሉ ላይ እንደሚገኝ አረጋግጧል። ይህም የሰሜን ኮሪያው መሪ ከ2019 ወዲህ ወደ ቻይና የሚያደርጉት የመጀመሪያ ጉዞ ይሆናል።
ከ2011 ጀምሮ ስልጣን ላይ ከወጡ በኋላ 10 የውጭ ሀገር ጉዞዎችን ብቻ ያደረጉት ኪም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ብቻቸውን ከአገራቸው የወጡት በ2023 ሩሲያ ምስራቃዊ ጫፍ ላይ በሚገኝ የጠፈር ማስወንጨፊያ ማዕከል ውስጥ ከፑቲን ጋር ተገናኝተው ነበር።
ይህ ትርኢት በዓለም ላይ በከፍተኛ ደረጃ ማዕቀብ የተጣለበት የሰሜን ኮሪያ መንግስት፣ ዢ እና ፑቲን ለመፍጠር እየገፉበት ባለው አማራጭ የዓለም ስርዓት ዙሪያ እየተሰባሰቡ ካሉ ሌሎች የዓለም መሪዎች ጋር አብሮ ለመስራት ያስችለዋል።
ኪም በትርኢቱ ላይ እንደሚገኝ የተረጋገጠው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዚህ ዓመት የሰሜን ኮሪያውን መሪ ማግኘት እንደሚፈልጉ ከተናገሩ ከጥቂት ቀናት በኋላ ነው።
