የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት እንደሚያመላክተው በሩብ ዓመቱ 3ሺ32 የፍቺ ምዝገባ መከናወኑን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሴ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በሩብ ዓመቱ በወሳኝ ኩነት ምዝገባ 153ሺ787 ልደት ምዝገባ ተከናውኗል። 25ሺ876 ህፃናት በተወለዱ በዘጠና ቀናት ውስጥ የተመዘገቡ ሲሆን 4ሺ194 ደግሞ በአንድ ዓመት ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በተጨማሪም 10ሺ696 ጋብቻ በሩብ ዓመቱ ተመዝግቧል።እንዲሁም 100 የጉዲፈቻ ምዝገባ መከናወኑን ገልፀዋል።
4ሺ396 የሞት ምዝገባ በወቅታዊ፣በዘገየ እና የጊዜ ገደቡ ባለፈ ተመዝግቧል ።እንደ አጠቃላይ በበጀት ዓመቱ የ1ኛ ሩብ ዓመት ውስጥ 172ሺ011 ምዝገባ በማድረግ ከእቅድ በላይ ማከናወን መቻሉን አቶ ዮሴፍ ንጉሴ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
